
በፌደራል መንግሥት አማካኝነት በትግራይ ክልል መረጋጋትን እና ቀጣይነትን ለማረጋገጥ ሰፋ ያለ የምክክር ሂደት ሲከናወን ቆይቶ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተደርጓል።
በዚሁ ወር የሚኒስትሮች ምክር ቤት የዘጠኝ ወራት የአፈፃፀም ግምገማም ተካሂዷል። ግምገማው በቁጠባ እና ኢንቬስትመንት አንፃር በሰፊው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ጥረት የታየውን አበረታች አዝማሚያ ተመልክቷል። የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሀገራዊ ቁልፍ ጉዳዮች እንዲሁም በፓርቲ ተኮር ጭብጦች ላይ ውይይት አድርጎም ውሳኔዎችን የተተላለፉበት ወር ነበር። ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ሚያዝያ 1 ቀን 2017 ባደረገው ስብሰባ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ገምግሟል፡፡
በአለምአቀፉ መድረክም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በቬይትናም ይፋዊ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ከሀገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋርም ውይይቶች ተደርገዋል። ጉብኝቱ በንግድ እና በትምህርት ሁለት የመግባቢያ ሰነዶች እንዲፈረሙ እድል ፈጥሯል። ከአዲስ አበባ ሃኖይ የቀጥታ በረራ እንዲኖር የሚያስችል የሲቪል አቪየሽን ስምምነትም ተፈርሟል። በፒ4ጂ ቬይትናም ጉባኤ 2025ም ኢትዮጵያ አምስተኛውን የ2027 ጉባኤ ለማስተናገድ ችቦውን ተረክባለች።
በሀገር ውስጥ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የካዛንቺስ የኮሪደር ልማት ክፍልን የመረቁ ሲሆን የመንግሥት አገልግሎቶችን በዲጂታል ትስስር የሚያቀርበውን የመሶብ የአንድ መዐከል አገልግሎትን ሥራ አስጀምረዋል። አዲስ የቡልቡላ ፓርክ ጨምሮ ከቡልቡላ አቃቂ ድልድይ የተዘረጋውን ቁልፍ የመሠረተ ልማት ሥራ ጎብኝተዋል። ለአካታች ማኅበራዊ እሴት ያላቸውን ፅኑ እምነት በሚያሳይ ሁኔታም የትንሣኤ በዓልን ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ካላቸው ዜጎች ጋር ማዓድ በመጋራት አክብረዋል።
እነሆ በሚያዚያ ወር የነበሩ ሁነቶች በምስል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.