
የኮሪደር ልማት በተመለከተ
👉በኮሪደር ልማት የመጣው
ለውጥ "አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታለን" ብለን ለህዝባችን ከገባነው ቃል የመነጨ ነው። ለአብነት የኮሪደር ስራችን ከመጀመራችን በፊት ባደረግነው ጥናት የአዲስ አበባ የመንገድ መሰረተ ልማት እና የአረንጓዴ ሽፋን እጅግ ከፍ እንዲል ያስቻለን ሲሆን ይህም ለከተማችን ነዋሪዎች አጠቃላይ ጤና ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑን ሁሉም የሚገነዘበው ጉዳይ ነው።
👉በኮሪደር ልማት መኪና መንገድ ብቻ ሳይሆን 80% በላይ ተሽከርካሪ የሌለውን የከተማችን ነዋሪዎች በቀላሉ ሊጠቀሙበት የሚችሉትን የእግረኛ መንገዶችን አስፋፍተናል የሳይክል መንገዶችንም ማስፋፋት በመጀመራችን ህዝቡ ተጠቃሚ ሆኗል።
👉 በኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ስራ የታየው ወሳኝ ጉዳይ የህዝባችን ያላሰለሰ ድጋፍና ትብብር የተረጋገጠበት መሆኑ ነው። በዚህ ስራ ውስጥ ወጣቶች እና ሴቶች በጉልበታቸው አግዘዋል፤ ባለሀብቶች ገንዘባቸውን አፍስሰዋል፤ የልማት ተነሺዎች አስደናቂ ትብብር አድርገዋል።
👉ኮሪደር ልማቱ የከተማችንን ገፅታ መቀየሩ እና ለህዝባችን ምቹ መኖሪያ እንድትሆን ከማድረጉ ጎንለጎን ለበርካታ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ፈጥሯል።
👉 የከተማችን ነዋሪዎች ልማቱ ወደ ሁሉም የከተማችን አካባቢዎች እንዲመጣ መጠየቃቸው አግባብነት ያለው ጥያቄ ቢሆንም ስራው ሰፊ ሀብት እና ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ በጥናት እና በቅደም ተከተል ወደ ሁሉም የከተማችን ክፍሎች በመምጣት የምናለማ ይሆናል::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.