ማህበራዊ ችግር ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ማህበራዊ ችግር ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ከተረጂነት ባለፈ በቂ ስልጠና በመስጠት መስራት የሚችሉትን የማሸጋገር ስራ ሰርተናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የኑሮ ውድነትና ጫናን ለማቃለል አለሜቀፋዊ ሁኔታን አገናዝበን ምላሽ ለመስጠት ሞክረናል።

* ኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ አቅርቦትን ማሳደግ ላይ በትኩረት በመስራት በአምስቱም የከተማችን መግቢያ በሮች የግብርና ምርቶችን አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግና የደላሎችን ሰንሰለት መበጣጠስ ችለናል።

* የኑሮ ውድነት ችግርን ማቃለል የምንችልበት መንገድ አምራችነትን በማሳደግ እንደመሆኑ መጠን የከተማችን ነዋሪ በተለያዩ አግባባች አምራችነቱ እንዲያድግ ስልጠና የመስጠትና የግብአት አቅርቦት እገዛ እያደረግን ነው።

* የገበያ ማረጋጋት ስራን በተመለከተ በቁጥጥር፣ በክትትልና፣ በድጎማ ህቦረተሰባችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራን ነው።ውጤትም አግኝተንበታል።

* ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችና የእናቶችን የኑሮ ጫና ለማቃለል የሰራነው ስራ ሁሌም የምንኮራበት ነው።

* 26 የምገባ ማዕከላን  በመክፈት ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመመገብ ፍትሀዊ ተጠቃሚነታቸዉን ከማረጋገጥ ባሻገር ዜጎች አብሮ የማደግ ባህል እንዲጎለብት አድርገናል።

* 2 የገበያ ማዕከላት ተጨማሪ እየተሰራ ነው በቅርቡ ስራ ይጀምራሉ::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.