
ኢ/ር ወንድሙ ሲታ በም/ከንቲባ ማአረግ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ
👉የከተማዋን የፍሳሽ ማስጋጃ ስርዓት የማዘመንና በአዲስ መልከ የመገንባት ስራ በስፋት እየተከነወነ ይገኛል፡፡
👉የአደጋ ስጋት ተጋላጭነትን ለመቀነስ በልዩ በትኩረት አካባቢዎችን በመለየት እየሰራ ነው፡፡
👉የቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት ላይ ያመጣነው ለውጥና ያስገኘነው ውጤት በከተማችን ገፅታ ላይ ግልፅ ለውጥ እያመጣ ነው::
👉ቆሻሻን ወደ ኢነርጂ ከመቀየር አንፃር አሁንም የሚቀሩን ስራዎች አሉ፤ የከተማዋን ፅዳት አረጋግጠን ቆሻሻን ወደ ኢነርጂ መቀየር ላይ በትኩረት መስራት ይኖርብናል።
👉ከውሃ ፍትሃዊ ስርጭት አንፃር 377,000 ሜ.ኪዩብ ውሃ የማምረት አቅም በማጎልበት ተደራሽነታችንን ለማሰደግ የተሰራ ሲሆን በቀጣይ 100,000 ሜ.ኪዩብ ተጨማሪ የውሃ አቅርቦት አቅም ለመፍጠር በትኩረት እየሰራን ነው::
👉የመብራት መቆራረጥ ችግር መንስኤዎች በነባር መንደሮች ያለውን አሮጌ መሰረተ ልማት ጋር የተገናኘ በመሆኑ በቀጣይ የመብራት ሃይል አቅርቦት መሰረተ ልማትን በአዲስ መልክ ለመገንባት በማስተርፕላኑ ውስጥ ማስገባት በዘላቂነት ለመፍታት ያግዘናል ፡፡
👉የኮሪደር ልማት ሰራችን ይህንን የመሰረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ በሚያስችል መልኩ እየተሰራ ይገኛል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.