.png)
ትናንት ሚያዝያ 22፣ 2017 ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር አብረው የቡልቡላ ፓርክን በጎበኙበት ወቅት ከተናገሩት:-
"ይሄን ሁሉም ክፍለ ከተማ መማር አለበት:: በራስ አቅም ህዝብን አስተባብሮ እንዲህ ያለ ስራ መስራት ያስፈልጋል."
ከቦሌ ኤርፖርት ካርጎ ቡልቡላ እስከ አቃቂ ድልድይ በራስ አቅም የተገነባ ከ20 ሄክታር በላይ የሚሸፍን ስራ የተሰራ ሲሆን ይህም የቡልቡላ ፓርክን ጨምሮ የአረንጓዴ ሥፍራዎች ፣ የመንገድ አካፋይ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳዎች እንዲሁም በርካታ መሠረተ ልማቶች የተሰሩበት ሥፍራ ሆኖ ይገኛል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.