የከተማ አስተዳደራችን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የከተማ አስተዳደራችን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጀምሯል።

በግምገማ መድረካችን ያለፉት ዘጠኝ ወራት ስኬታማ ስራዎችን በመፈተሽ ጥንካሬዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል ዝርዝር ግምገማ የምናደርግ ሲሆን፣ ታቅደዉ ያልተፈፀሙ እና በስድስት ወራት የስራ ግምገማችን ወቅት በዝርዝር ለይተን በሰጠነው ግብረመልስ እና አቅጣጫ መሰረት የህዝብ የቅሬታ ምንጭ የሆኑ ክፍተቶች አፈታትን በጥልቀት የምንገመግም ይሆናል።

በተጨማሪ በመድረኩ የአመራራችንን ችግር የመፍታት አቅም፣ የሚመራውን ተቋም ክፍተት በመለየት ምን ያህል ማሻሻል እንደቻለ እና ክፍተቶችን አስቀድሞ ለይቶ በፍጥነት መፍታት ላይ የመጡ ለውጦች ይገመገማሉ።

የግምገማ መድረኩ በቀሪ ሶስት ወራት እቅዶቻችንን በተሟላ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስችሉ መግባባቶች ላይ የምንደርስበት ሲሆን፣ የለየናቸዉን ክፍተቶችን በማረም ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት ለማገልገል ራሳችንን ይበልጥ የምናዘጋጅበትም ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.